bridgethoughts | Unsorted

Telegram-канал bridgethoughts - ድልድይ | Dildiy | Bridge

-

“Let's build bridges, not walls.” Martin Luther King, Jr. — Visit my blog: https://dildiy.net/ — ድልድይ - ግላዊ እይታና ጥልቅ የመሻገሪያ እሳቤዎች የሚጋሩበት ከንባብ፣ ከኑረት እና ከምናብ የሚቀዱ ንሸጣዎች መድረክ ነው። - ሃሳቦቹ ከየትኛውም የአስተሳሰብ ጎራ (ism) አይወግኑም!! — Concern & Concept — D.S.

Subscribe to a channel

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

አስተውለህ ታውቃለህ?...


ለብዙ ችግሮቻችን የምናደርጋቸው ጥንቃቄዎች ዕድሜ ሰከንዶችን አይሻገርም፤ 


ሆኖም


በትዕግስት ማጣትና ቸልተኝነት ሰበብ የሚወለድ መዘናጋት ግን በዓመታት የማይሽር መዘዝ ያመጣል...


[Keep this in mind...]


✨✨✨


መኪና መንገድ ለማቋረጥ ጥቂት ሰከንዶች መታገስ ይበቃል - በምንግዴ ዘው ካሉበት ግን ከአካል ጉድለት እስከ ሥጋ ሕልፈት የሚደርስ ዋጋ ያስከፍላል... 


[አረንጓዴው መብራት በቀይ እስኪተካ ስለቆምክ ዓለም አታልፍም... እዚያስ ሄደህ ልትቀመጥ አይደል?...]


✨✨✨


የሲሊንደሩ ጋዝ ማፈትለኩን ለማረጋገጥ ለሰከንዶች ማሽተት ይበቃል - ይህን ሳያደርጉ ክብሪቱን መጫር ግን ለአካል ጉድለትም ለንብረት ውድመትም ሰበብ ይሆናል...


[ምግቡ እስኪበስል መቆየትህ ይቀራል?...]


✨✨✨


የቁጣን ስሜት ለመቆጣጠር ሰከንዶችን መታገስ በቂ ነው - ቸኩሎ እርምጃ መውሰድ ግን ዓመታት ለሚሻገር ጸጸት ሰበብ ነው... ለመገንባት ረጅም ጊዜ የወሰደን ወዳጅነት ለማፍረስ ምክንያት ነው... ዘብጥያ ወርውሮ ተስፋን ለማጨለም በቂ ነው...


[በምላስ ተናግሮ ከማስቀየም በትንፋሽ ተቆጣጥሮ ማለፍ አለ... ተኩሶ ከመግደል ይቅር ብሎ መዝለል አለ... ቸኩሎ ከመታሰር ታግሶ መከበር አለ...]


✨✨✨


እንዲህ እያልክ ብዙ ነገር ማሰብ ትችላለህ...


___

“One moment of patience may ward off great disaster; one moment of impatience may ruin a whole life.” — Chinese Proverb


ብቻ...


ጥቂት ጊዜ - የብዙ ጊዜ ደስታ መነሻም፣ የዕድሜ ልክ ህመም መቀስቀሻም ሊሆን ይችላል...


ችግሩ ግን... 


ወከባ ላይ ነን... ብዙዎቻችን ከምህዋራችን ውጭ በመጦዝ ነው ቀኖቻችን የሚያልፉት... ስክነት ይጎድለናል... በቂ አሁን የለንም... እንደምናስበው ከራሳችን ጋርም አይደለንም... የኑሮ አውታር በየአቅጣጫው ሰቅዞናል...


መላውሳ ምን ይሆን?... Stillness!!


[ትርጉም...]


በተረት -

✍️ 'የረጋ ወተት - ቅቤ ይወጣዋል'

በዜማ ስልት -

✍️ 'ያዋከቡት ነገር - ምዕራፍ እያገኝም'

በምሳሌ ውበት -

✍️ 'የቸኮለች - አፍሳ ለቀመች' 

___

"Patience is not resistance to time,
it is the silence of trust —
the knowing that what belongs to you
can never be lost in hurry.
When you stand still in awareness,
time itself becomes patient with you."

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

ከእያንዳንዱ ዕውቀት፣ ከእያንዳንዱ ተገንዝቦት፣ ከእያንዳንዱ መረዳት ጀርባ ግዙፍ ድፍረትና አይለኬ መስዋዕትነት አለ...


ዛሬ ላይ ባሕር ውስጥ ስላለው ዓለም ያለን ዕውቀት በብላሽ አልደረሰንም... አደገኛ በሆኑ የውሃ ሰርጦች፣ አሳነባሪና ሻርክ በሚራኮትባቸው ጥልቆች፣ ማዕበልና ወጀብ በሚንጣቸው ዳርቻዎች ላይ ለመገኘት የደፈሩ ጥቂት ሰዎች በከፈሉት ዋጋ እንጂ...


ስለ ጠፈር የምናውቀው ሁሉ በምቾት ውስጥ አልተገበየም... የምድርን ድሎት የናቁ፣ ጽልመትና ፀጥታን የደፈቁ፣ ማንም ካልደረሰበት ሕዋ በድፍረት የመጠቁ ሰዎች የማይተመን ዋጋ ከፍለው እንጂ...
 

በባዮሎጂ መነጽር የስነ-ሕይወትን ዕውቀት፣ በኬሚስትሪ ጉልበት የነገረ-ውህደትን ውጤት፣ በፊዚክስ ምጡቅ ዓይን አይዳሰሴውን ጥልቀት፣ በምህንድስና መሰረት ውስብስቡን ግንኙነት ተረድተናል... ለዚህ ሲባል ግን - ጥቂቶች ቀንና ሌት መድከም ነበረባቸው፣ ትጉሃን በእሳት ላንቃ መለብለብ ነበረባቸው፣ ለዕውቀት ጥራት መውደቅ ነበረባቸው፣ አሰልቺ ሰዓታትን በዝግ ውስጥ ማሳለፍ ነበረባቸው...


በታሪክ፣ በፍልስፍና፣ በሕግና ፖለቲካ እንረቅ ዘንድ ጥቂቶች ብጥስጣሹን ገጣጥመዋል፣ ቆራጦች የሻገቱ መዛግብትን አገላብጠዋል፣ ጽኑዎች በኑረት ትግል ውስጥ ቀልጠዋል... ስለ እልፎች ደስታ ተነጥለዋል፣ ስለ ሚሊዮኖች ምቾት ተሰደዋል፣ ስለ ቢሊዮኖች አብርሆት ሁሉን በድፍረት ጠይቀዋል...


የተዝናኖት ምንጫችን ስነጽሑፍ፣ የነፍስያ ቋንቋችን ሙዚቃ፣ የምናብ ሜዳችን ስነ-ጥበብ በገባን ልክ የታወቀው እረፍት አልባ ነፍስ ባላቸው የጥቂቶች ጥረት ነው... እነርሱ ውብ ድምፃቸውን፣ የንስር ዓይናቸውን፣ ብሩካን እጆቻቸውን ስለሰጡን በዘመናት ውስጥ ስለሚሻገር ውበት አወቅን...


ብዙ መውደቅ መነሳት - መድኃኒትን፣ ብዙ ሕመምና መገፋት - ስነልቡናን፣ በጽናት የመቆም ትጋት - ማሕበራዊ ሳይንስን እንድናውቅ አድርጎናል...  


ብዙ እንቅልፍ አልባ ለሊት፣ እልፍ ተስፋ አስቆራጭ ሙከራ፣ ገደብ የለሽ ደምና ላብ - ቴክኖሎጂን ለግሶናል... ሰውን የማፍቀር ሃሌታ፣ ህብርም የመፍጠር ከፍታ ኢንተርኔትን ሰጥቶናል...






ተ....

___

እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ በግዙፋን ትከሻ ላይ ቆመን የሩቅ ጉዞን የምናልም፣ ሆኖም ለትከሻው ድካም ለአፍታ ዋጋ መስጠት የማናስብ ቸልተኞች ነን...


We take everything for granted...

___

አስገራሚው ታዲያ...

አንድ ሰው 'ጎበዝ' የሚባለው የዕውቀት ምንጭ በመሆኑ ሳይሆን ዕውቀትን በማነብነብ ኃይሉ ነው... ዕውቀት በማከሉ ሳይሆን ዕውቀት በመገልገሉ ስልት ነው...


አስታውስ...


የትምህርት ስርዓታችን የሚያነግሰው አስታውሰው የመለሱትን እንጂ አሰላስለው የጎለመሱትን አይደለም...


በዚህ ምክንያት ዕውቀት ባልተገባ ተገንዝቦት አዋቂና ቃራሚ የሚምታታበት እሳቤ ሆኗል...


ምናልባትም...


አዋቂው 'አዋቂ ነኝ' ሳይል፣ ቃራሚው 'ከእኔ በላይ ላሳር' የሚያበዛበት መድረክ እየሆነ ይመስላል...


ልክ እንደ ምሳሌው...


'በአትክልት እርሻ ውስጥ ፍሬ የያዙ ተክሎች አንገታቸውን ይደፋሉ፤ ፍሬውን የሚበሉት ወፎች ግን ከፍ ባለ ድምጽ ይንጫጫሉ...'

___

ክብር... ዓለምን በየቅጽበቱ ለሚያድሷት ጠቢባን!!

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

አንቺ የሌለሽበት...

[የድልድይ የሙዚቃ ግብዣ]

___
@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

በዓለም ታሪክ አንድም ሃገር ጦርነትን አሸንፎ አያውቅም!... አንድም ሃገር!!...


የመስተጋብራችን ታሪክ በተሸከፈባቸው ባለፉት ብዙ ሺህ ዓመታት በምድራችን ላይ ብዙ የጦር አውድማዎች ተፈጥረዋል... የሰው ልጅ ሳይሰለች ጦር ተሳብቋል፣ ሳያሰልስ ተሞሻልቋል፣ ያለፋታ በባሩድ ጢስ ታጥኗል፣ በጥይት ጫፍ ህልም ቀጥፏል...


[ጦርነትን ግን አሸንፎ አያውቅም...]


ከባሕላዊ እስከ ዘመናዊ፣ ከእግረኛ እስከ አየር በራሪ፣ ከሃገር ድንበር እስከ ባሕር ተሻጋሪ፣ ከፊት ውጊያ እስከ ስውር ግፊያ - ተራቀቅሁ ባለባቸው መሳሪያዎች ሁሉ - የሰው ልጅ እስኪበቃው በራሱ ላይ ዘምቷል...


[ግን ጦርነትን አሸንፎ አያውቅም...]


የዓለሚቱ ጭካኔ ቅጥ አጥቷል... ጭቆናና የበላይነት የምድርን መልክ አጥፍቶታል... መግፋት፣ መንቀል፣ መግደል ተራ ጉዳዮች እየሆኑ ነው... በእያንዳንዱ ሰከንድና ደቂቃ ነፍሶች ይረግፋሉ... በእያንዳንዱ የዓለም ዳርቻ ሰቆቃ ይንበለበላል...


“In modern war, you will die like a dog for no good reason.” – Ernest Hemingway


አንዱ ሌላኛውን በብርቱ ያስጨንቃል... በመሪ እብሪት ታዝሎ እንባ ደም ያፈሳል... ግጭት ከመቀስቀስ እስከ መንግስት ማፍረስ፣ በቦንብ ከማውደም እስከ መሪ መሾም፣ ዜጋን ከገዛ ሃገሩ ከማባረር ሌላ ሃገር እስከ ማስፈር - የማንሰማው ጉድ የለም... ገራሚው ግን ይህን ሁሉ ሃይ የሚል አለመኖሩ ነው... ዜጎችን ከእብሪተኞች ጡጫና ከእብዶች እርግጫ የሚከልል የዓለም ስርዓት የለም... የሃገራትም ሆነ የዜጎቻቸው ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በመሳሪያ አምራቾች ምርጫ ነው...


ጥቂት የገንዘብ ብቻ ሃብት ያላቸው ሰዎች ኪስ እንዲሞላ በየቀኑ የጥይት ናዳ፣ የከተሞች ጎድጓዳ፣ የንጹሃን ዕዳ የማይተዋቸው ሃገራት ይኖሩናል... ከስልጣናቸው መክረም ውጭ አንዳች የሚሻገር ህልም በሌላቸው አምባገነን መሪዎች ቅዠት - እንቦቃቅላ ሕፃናት በጥይት ይረግፋሉ፣ ተስፋ ያላቸው ወጣቶች ይማገዳሉ፣ አዛውንቶች በየጎጆው ይደፋሉ...


[ያም ሆኖ ዛሬም ድረስ ጦርነትን አሸንፎ የሚያውቅ የለም...]


አፍሪካ በራሷ ልጆች አንገት ላይ ካራ ትሰካለች... በድሃ አደግ ሕዝቦቿ ላይ የደም አበላ ታወርዳለች... ከሰሜን ከፍታ እስከ ደቡብ ዝቅታ፣ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ አጽናፍ - ሰላም ጸንቶ አያውቅም... ፍቅር አይሰነብትም...


የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመት ባላቸው ጉጉት ታውረው ልጆቿን በእልፍ ጎራ ከፍለው ያተጋትጓታል... ለዚህኛውም ለዚያኛውም ልጇ መሳሪያ ያቀርቡላታል... ለዚህኛውም ለዚያኛውም አካሏ አማካሪ ይሆኗታል... እርሷ እንቅልፍ ላይ ናት... ሴራ አታስተውልም፣ ስራይ አትገነዘብም... ዜጓቿ ሰርቶ መኖር፣ ገብቶ መውጣት፣ ተምሮ መለወጥ ሲያምራቸው ይቀራል እንጂ ጥቂቶች ኪሳቸው እስከሞላ፣ ሆዳቸው እስከቀላ ድረስ ግድ አይሰጣትም...


[ዛሬም ድረስ አፍሪካ የውስጧን ጦርነት አሸንፋ አታውቅም...]


በየመዳረሻው የሰው ልጅ በረሃብ ያሸልባል፣ በጠኔ ይረግፋል፣ በጥም ይጠወልጋል... 


ግጭት የማያውቀው፣ የጦርነት አለንጋ የማይገርፈው፣ የጥይት አረር የማያስደነብረው አንድም የዓለም ጥግ የለም... ጦርነትና ግጭት የሰው ልጅ ቋሚ ልማድ ሆኗል...


ዜጎች በገዛ ቤታቸው በሰላም አይተኙም... በገዛ ምድራቸው ተረጋግተው አይኖሩም... በዕጣ ፈንታቸው ላይ አይወስኑም... የኔ የሚሉት አንድም ዋስትና የላቸውም... ነቃይና ተካያቸው ጉልበተኛው ነው... 


“If we have no peace, it is because we have forgotten that we belong to each other.” – Mother Teresa


ሃገር በሌላ ሃገር ላይ እጅ ታነሳለች፣ መንግስት በዜጎቹ ላይ በእብሪት ይኮፈሳል፣ ክፉው ከወገኑ መከራ 'ሲሳይ' ያፍሳል...


በጣም የሚያስደነግጠኝ ብዙ ደካሞች በጥቂት ጉልቤዎች ስር መጨፍለቃችን አይደለም... ጭፍለቃውን justify የሚያደርግ አመለካከት ማዳበራችን እንጂ...


አዎን ጦርነትን የተለማመደ ትውልድ እየፈጠርን ነው... ከሌሎች እንባ የሚመነጭን ጥቅም፣ ከደማቸው የተላቆጠን ሃብት -  'አርበኝነት'፣ 'ብሔራዊ ጥቅም'፣ 'የሃገር ፍቅር' ፍቅር እያለ የሚያንቆለጳጵስ ድንዛዜ ውስጥ እየገባን ነው... ጦርነትን ምክንያታዊ ለማድረግ የምንሄድበት ርቀት ደግሞ ከጦርነቱ በላይ ያስፈራል...


“There is no flag large enough to cover the shame of killing innocent people.” – Howard Zinn


በዚህ የዓለም ስሪት ውስጥ ነገ የሚባለው ተስፋ ሁሌም የማይዳሰስ ነው... ሟችና በማንኛዋም ሰከንድ ውስጥ ተሰናባች መሆንህ የተፈጥሮ ድንጋጌ ቢሆንም ነቃይህ ከተፈጥሮ ቅኝት ውጭ የሚጓዘው እብሪተኛ መሆኑን ማሰብ ያደክማል...

___

የድልድይ አቋም...

.
.
.

ሃገር - ተፈጥሮ ከለገሳት፣ ድካሟም ከቸራት ሁሉ እንዳትበላ የሚያደርጋትን ማንኛውንም ኃይል መቃወም ጤነኛ ተግባር ነው... እያንዳንዱን ችግር ጦር መዞ፣ ሳንጃ ደቅኖ መጋተር ግን ብልህነት አይሆንም...
 

ዛሬ በጦር አስገብረህ የምታገኘው ነገር ለነገው ትውልድ የሌላ ዙር ጦርነት ሰበብ እስከሆነ ድረስ ጦርነቱን አላሸነፍከውም... የዛሬ ኃይልህ ለነገ ሰላም ዋስትና ካልሰጠ ያንተን ስግብግብነት እንጂ ለልጅህ ያለህን አሳቢነት አያመለክትም...


“Wars are poor chisels for carving out peaceful tomorrows.” – Martin Luther King Jr.


'ለልጄ የበቀል አዙሪት አላስቀምጥም' ያሉ ዛሬን ያስገብራሉ፣ ነገንም ያሸንፋሉ... 


ያልተሄደበትን መንገድ ደፍረው መሻታቸውን የሚፈጽሙ ሃገርን ይወዳሉ፣ ለትውልድ ይጨነቃሉ... 


'ልጆቼ ላይ ዕዳ ጭኜ አልሄድም' ያሉ በአስተዋይ ውሳኔያቸው ብርታት በትውልዶች ይዘከራሉ...


አዎን...


ጦርነትን ያሸነፉት ጦርነትን ያስቀሩት ናቸው...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

✨አልከራማ - ባለቤት አልባው ጎጆ ✨

.
.
.

በቤንሻንጉል ኮረብቶች፣ በበርታዎች መንደር ውስጥ - የየትኛውንም ትውልድ አንደበት ትንግርት የሚያስብል ተግባር ይከወናል... በጸጥታ፣ በስውር፣ በድብቅ... 


ነገሩ ምን መሰላችሁ?... 


በርታዎች በነፋሻማዎቹ መመላለሻዎች ዳርቻ፣ ከተጓዥ መተላለፊያ መንገዶች ግራና ቀኝ ትናንሽ ቤቶችን ይገነባሉ... ለመኖሪያ አይደለም፣ ለንግድም አይደለም፣ ለመንገደኛ እንጂ...


ተሾመ ገ/ሥላሴ 'የባሕር ጠብታ' በተሰኘ የግጥም መድብሉ መግቢያ ላይ [በርታዎች በዚያች ቤት ውስጥ] "... ምግብ፣ ውሃ፣ የመስገጃ ምንጣፍ፣ ቡናና ከሰል ያስቀምጣሉ... ቤቱ የማንም አይደለም... የእንግዳ ቤት ነው... የራበው መንገደኛ [ምግብ] በልቶ፣ [ውሃ ጠጥቶ]፣ አርፎ ይወጣበታል... ማንንም ማመስገን አይጠበቅበትም..." በማለት በሁለት መስመር ብርታት የባሕሩን ግማድ ያሳየናል...


የቤቱ ስም 'አልከራማ' ይባላል... እናንተ 'የአብርሐም ቤት' ልትሉት ትችላላችሁ... የልግስና ታዛ፣ የደግነት አምድ ቢባልም ትርጉሙ ያው ነው... ትልቁ ቁምነገር ግን በቤቱ ውስጥ የምናገኘው ምግብና መጠጥ አይደለም - ከዚያ ጀርባ ያለው የመንፈስ ንጽሕና እንጂ... ባለቤት አልባ ቤት፣ ቀኙ 'ሚሰጠውን ግራው የማያይበት ልባም፣ ምስጋና ሽቶ ከታዛው ያልተቀመጠ ለጋሽ፣ በጸጥታ - በዝምታ - በአርምሞ የሚቸር ስጦታ... በክብረት - በከፍታ - በምልዓት የሚመለስ ውለታ...


[አዎን - ዛሬም ድረስ መንገድ መንገደኝነቱን አልተወም... ተጓዥም ደረስኩ ብሎ መጓጓዝ አልቀረም...]


አልከራማ ከቤትነት የምትሻገር ከፍታ ናት... የጥልቅ ፍልስፍና ሰንዱቅ፣ የልግስና ምጡቅ፣ የሰብዓዊነት ረቂቅ ናት... አማናዊው ስጦታ በእውቅና የማይመተር፣ በውለታ የማይታሰር፣ መቀበል ሳይጠብቁ መቸር መሆኑንም ታስተምረናለች... 


🔥 መስጠት ግን ሰጪ ሆኖ አለመገኘት - መሄድ... 
🔥 መድከም ግን ድካምን አለማወጅ - ራስ መካድ...
🔥 ማስቀመጥ ግን ጠባቂ አለመፈለግ - ማመን...


[ይገርማል!!...]


እንኳን ማዕድ አኑረህበት የእከሌ የማትለው ባዶ ቤት በግላጭ መገኘቱ፣ ማሕበረሰቡ ይሆነኝ ብሎ አልከራማን መገንባቱ - ብቻውን ድንቅ ነገር ነው... 


አዋጅ ሳይነገር ምንም በማይደረግባት ሃገር ውስጥ ድምጹን ሳያሰማ ሹልክ ብሎ ገብቶ - ለሆድ የበሰለውን፣ ለጥም የሚያረካውን የሚያስቀምጥ ንጹህ ልብ መገኘቱም አስገራሚ ነገር ነው... 


[እስኪ አስበው...]


🌼 ከተሜ እኮ ለለቅሶ ቤት እንኳ እራት የሚወስደው የዕድር ሰብሳቢዋ ስታዘው ነው... እነርሱን ማን አስገደዳቸው?... 


🌼 እዚህ ሃገር በራስ ድልም ሆነ በሌላው ድካም ስሜ ካልገነነ ባይ ብዙ ነው... መደበቅን ለእነርሱ ማን ነገራቸው?... 


🌼 በተስኪያን ተገኝቶ 'ምጽዋቴ በድምጽ ማጉያ አልተነገረም' ብሎ የሚከፋው፣ በደመወዝ እየሰራ ውለታ የዋለ የሚመስለው፣ ያበደረህን መልሰህ እንኳ አኮቴት የሚጠብቀው፣ ወዘተ - እጅግ ብዙ ነው... ውለታ ሳይጠብቁ ቅንነት መዋልን ማን አስተማራቸው?...


[ልብ አድርግ...]


የለመነንን አይተን ያለንን መስጠትና ለማያውቁት ሰው በማይታወቁበት ሁኔታ ደግ መሆን የተለያዩ ነገሮች ናቸው... በሌህበት ድርጊትህ ብቻ ሲገኝ 'ጠላቴ' የምትለውን ሰው ሳይቀር ሊጠቅም ይችላል... ቤትህ መጥቶ የለመነህ ግን በአኳኋኑ ብቻ እጅህን ሊያሰበሰብ ይችላል...


[አልከራማ... የደግነት ማማ!!]


ይህ ዓይነቱ ልምምድ በሱፊዎች መንደር የተለመደ ነው... እነርሱ ጋ መንገደኞች ስውር አገልጋይ አላቸው... በበረሃ እዚህና እዚያ በተሰሩ ታዛዎች፣ በከተሞች ውብ ተደርገው በተሰሩ ማረፊያዎች ይስተናገዳሉ... ማዕድና ቀዝቃዛ ውሃም ያገኛሉ... [አይከፍሉም - ሻጭ ከባንኮኒው የለም... ስም አይጠየቁም - ተቆጣጣሪው ከበር አልቆመም...] ለእነርሱ የማያውቁትን እንግዳ ማስተናገድ መለኮትን በሰው አምሳል ማገልገል ነው...


አዎን - ታላቁ ስጦታ ምላሽ የማይጠብቁበት ነው... ይህ ችሮታ ተናጥሎን አያውቅም - ተጓዥ እና ለጋሽ፣ መንገድና ታዛ፣ [ማዕድ ያኖሩ ልቦች፣ የተቀበሉም እጆች] - በአንድ ነጠላ ክር ይዳወራሉ... በፍቅር!!...


[ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ!!...]


___

ወጋችንን ከሱፊዎች መንደር በተዋስናት ውብ መስመር እንቋጭ:


“The water does not drink itself, the tree does not eat its own fruit, the sun does not shine for itself. To live is to give.”

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

እነርሱ - በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር ቆይተው የባርነት አባዜ ባይተዋቸው ወራሪዎቻቸው የፀነሱት 'ስምምነት' ጸንቶ ይግዛን ይሉናል...


እኛ - በአባቶቻችን የደም ዋጋ በነፃ ሃገር ተወልደን ጌትነት ስለተቀዳጀን በራሳችን ጉዳይ ላይ ለመወሰን እኛ እንበቃለን እንላለን...


The difference is visible!!


ኢትዮጵያ... 


[አባይ ወንዟና የታሪክ ጓዟ ጎስቋላ ያደረጓት ሃገር ነች...]


ዛሬ በአባይ ወንዟ ላይ ሰልጥናለች - ነገ በታሪክ ሰበብ የተጣባትን ቀውስ ትፈታለች...

.
.
.


አዎን...


📯 የሚጀምር ትውልድ አባል መሆን ደስ ይላል!

📯 ሂደት የሚመራ ትውልድ አካል መሆን ደስ ይላል!

📯 የሚጨርስ ትውልድ አባል መሆን ደስ ይላል!

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

ባስነጠሰ ቁጥር ፈሱ የሚያመልጠው ሰውና የወር ደሞዝተኛ ኑሮ አንድ ናቸው... 

Just saying...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

ዘወትር እሁድ ምሽት ከሩቅ የሚሰማኝ አንድ ሙዚቃ አለ... የሚስረቀረቅ፣ የሚስለመለም፣ የሚያባባ ዓይነት... 


ግጥም የለውም... ዘፋኝ የለውም... የመሳሪያ ብቻ ሙዚቃ ነው... የጊታር፣ የክራር፣ የዋሽንት፣ የሳክስ፣ የቫዮሊን... [ቆይ ተውት - የመሳሪያውን ስም አላወቅሁትም...] 


ስሰማው እንባዬ ይመጣል... ባር ባር ይለኛል... ጭብጥ እላለሁ... ድምጹ የሩቅ ነው... አንዳንዴ ወደ ደጅ ወጥቼ የድምጹን አቅጣጫ አስሳለሁ... ግራና ቀኝ ከጎረቤት - አይደለም... ሽቅብ ሰማይ ቁልቁል መሬት - አይደለም... ምንጩ የት ነው?...


ዛሬም እንዲሁ ሆነ... 


አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ እየሰማሁት ቁልቁል እንባዬ ወረደ... እንደተለመደው ወጥቼ ከበሬ ቆምኩ... ጆሮዬን አዟዙሬ ቀሰርኩ... ምንጩን አላወቅሁትም... ከግቢ ወጥቼ ዞርዞር አልኩ... ስልኬን አውጥቼ Shazam ላደርግ ሞከርኩ... ሞባይሌ ድምጹ አልተሰማትም... [ሙዚቃውን ላገኝ አልቻልኩም] አለችኝ...


ወደ ቤቴ ገባሁ... 


የዚህ ሙዚቃ ምንጭ የት ነው?... ማድመጤን ቀጠልኩ... ዜማው አልተለወጠም... ውበቱ ግን አይሰለችም... ጣዕሙ ሁሌም አዲስ ነው...


ግራ ሲገባኝ ጆሮዬን ደፈንኩ... ግጥም አድርጌ በትራስ አፈንኩት... የሙዚቃው ጥራት ጨመረ... ጆሮዬን ከግንዱ ጋር ጨቆንኩ... ድምጹ ጭራሽ እየጎላ መጣ... 


በዚህ መሃል አንድ ድምጽ በሙዚቃው ስልት ውስጥ ሆኖ በለሆሳስ አናገረኝ...


ድምጹን አውቀዋለሁ... ያንተ ያለህ!... የራሴ ድምጽ ነው...


አንድ ቃል ብቻ ነው ደጋግሞ የሚነገረኝ...


'ትተኸኛል'... 

'ትተኸኛል'...

'ትተኸኛል'...


እንደ ሰማሁት ሲያውቅ እየሳሳ ሄደ... እየራቀ... እየራቀ...

____

✨ ለራሳችሁ ጊዜ ከሰጣችሁ ስንት ጊዜ ሆነ?... ከራሳችሁ ጋር ቁጭ ካላችሁ ስንት ጊዜ አለፈ?... በወግ ካወጋችሁ፣ ከተደማመጣችሁ፣ ሰከን ብላችሁ ከመከራችሁ - ምን ያህል ዓመት ሆነ?... ✨

____

“Nowhere you can go is more peaceful—more free of interruptions—than your own soul.” ~ Marcus Aurelius

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

የዛሬ ስንት ዓመት በእናትና አባቴ ጠያቂነት ምድሪቱ ከነገረ ስሪቷ የቆነጠረችውን ሥጋ በኪራይ አስረክባኝ በዚህች ውብ ዓለም ውስጥ ተከሰትኩ...


[የኑረት ስሌትህ እየገፋ ሲመጣ አባቶችህ ያስረከቡህን ስንቅ ቅርጥፍ አድርገህ ብትበላም ለልጅህ የምታቆየው ውርስ እጅህ ላይ አለመቅረቱ ስለሚያሳፍርህ ዕድሜህን አትናገርም...]


በኖርኩባቸው ዓመታት ሳቅና ለቅሶዬ ተላቁጧል... ደስታና ሃዘኔ ተጋምዷል... አክብሮት ንቀቴ ተሳስሯል... ፍቅር ጥላቻዬ ተቀይጧል... ማግኘት ማጣቴም ተዛንቋል...


እጅግ የረዘሙ ለሊቶች በጎጆ ጓዳዬ አቀርዝዘው ያውቃሉ... እጅግ አስደሳች ወቅቶችም በኑሮ ደጄ ተመላልሰው አልፈዋል... እጅግ የከፉ ሰዎች ሆዴን አሻክረው ያውቃሉ... እጅግ ልዩ ሰዎች ልቤን በሃሴት ሞልተዋል...


[የብዙ ሰዎች መዋጮ ነኝ...] 


ቆጥሬ የማልጨርሳቸው ሰዎች ቃላት የማይገዳደሩትን ውለታ እየዋሉልኝ ነው እዚህ የደረስኩት... ማወቅ ሳይገዳቸው እጅ የዘረጉልኝ፣ ስስት ሳይፈትናቸው በር የከፈቱልኝ፣ ምላሽ ሳይጠብቁ እልፍ የለገሱኝ - ብዙ ናቸው... ['የኔ የምለው አንዳች የለኝም' የምለው ለዚህ ነው]...


[መልካምነቴን እንጃ - እንጂ እኔም ብሆን ለሃዘናቸው ሰበብ፣ ለእንባቸው ምክንያት የሆንኳቸው አይጠፉም...]


ከደረሰብኝ ያልተናገርኩት ይንዛዛል... [ካልተናገርኩት የዘነጋሁት ይበዛል፣ ከተረፈው ውስጥ 'ይቅር' ያሟሟው ይገዝፋል]...


ያም ሆኖ...


እንቆቆ የጋቱኝ ማርነቴን አላጠፉትም... አይዞህ ያላሉኝ ብርታቴን አልነኩትም...


የገፉኝ ከገደል ወለል አልጣሉኝም፣ ወለል የጣሉኝ መውጫዬን መዝጋት አልቻሉም፣ ለመዝጋት ቋጥኝ ያኖሩ መብረሪያ ክንፌን አላዩም...


ሳይረዱኝ ለቀሩ ሰዎች ራሴን ላብራራ መድከሜ ያናድደኛል... ሳልረዳቸው ቀርቼ ያዘኑብኝን ሳስብ ይጸጽተኛል... [መተው ባይኖር - ከስረን ነበር]


የለመንኳቸው ሰዎች የተለማመጥኳቸው እንደመስላቸው ሲገባኝ ብስጭቴ ብቅ ትላለች... [ለመኖር ብዬ ግን አልተናነስም - ለመኗኗር ካልሆነ በቀር]... 


ግማሽ መንገድ ሊመጡ ሲገባቸው አልፌ የጠበኩዋቸው ሰዎች ግዴታዬ እንደሆነ ማሰባቸው ከገባኝ ድጋሚ አላገኛቸውም... በፍቅር ካደረጉት ግን እንደ ውለታ አልቆጥረውም...


ዝምታዬን ከሞኝነት፣ አንገት መድፋቴን ከሃፍረት ሲቆጥሩ በልቤ የናቅሁዋቸው አይጠፉም... ብልጣብልጥ መስዬ ከመንገዳቸው ግን አልወደቅሁም...


የአንዳንድ ሰዎች ክፋት አይሎ 'እንኳን አውላላ ላይ ጣሉኝ' አስብሎኝ ያውቃል... ምክንያቱም አማራጭ እንድፈልግ፣ አዲስ ሰው እንዳውቅ አድርጎኛልና...


___


የሆነስ ሆነና...


[ከመኖር ምን ተማርኩ?...]


☘ መተው! [እርግፍ አድርጎ መተው!]

☘ የኖረ ሁሉ ይሞታል! [ከውቅያኖሱ ላይ ወደላይ የወጣች የውሃ ጠብታ መልሳ ወደ ውቅያኖሱ ትቀላቀላለች]

☘ ይህም ያልፋል! [መፈራረቅ የገጽታ ደንቡ ነው]


___


እንኳንም ተወለድኩ... 


[ዛሬ የወጣችውን ፀሐይ ማን በእኔ አንፃር ያያት ነበር?...]

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

እንጂ
___

ማፍቀር አይደለም
ድንቁ፥
እንጂ
አፍቅሮ ማፍቀርን ማወቁ፥

መፈቀር መች ሁኖ ብልሃቱ
እንጂ እውቀቱ
ሲፈቀሩ፥ ፍቅር መሰማቱ፥

እውቀት አይደለም
ቁም ነገሩ፥
ጉዱ
እንዳወቁ ማወቁ።

___

ሰለሞን ዴሬሳ
/ዘበት እልፊቱ/
___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

'በቤትህ መስኮት በኩል ወጨፎ እየገባ ካስቸገረህ፣ ውሽንፍር ካፏጨብህ፣ ብርድ ካርገፈገፈህ... መስኮቱን መዝጋትህ የግድ ነው... ምንም እንኳ የውጭው ገጽታ ያማረ ቢሆንም...' ይላሉ...


በመኖር ውስጥም እንዲሁ ነው... 


ኑረት ብዙ ዓይነት ገጽታ ያላቸው ነገሮችን ከፊትለፊታችን ትገልጣለች... ሆኖም መስኮታችን መዘጋቱ ግድ ሊሆን ይችላል...  ገጽታቸው የሚያስጠላ ስለሆነ ግን አይደለም - ቀዝቃዛው ንፋስ ነባር ሰላማችንን እንዳያጎድል ስለምንሰጋ እንጂ...


አንዳንዴ የደስታ ምንጮቻችንንም እንደፍናለን... ጣፋጭ ስላልሆኑ ግን አይደለም - በጣዕማቸው ውስጥ የሸሸጉት ምሬት የኖረንን ጥፍጥና እንዳያጎድል እንጂ...


አንዳንድ ድልቀቃዎችን ባሉበት እንተዋለን... ዋጋቸውን ስለማንችል ግን አይደለም - ጤናና ክብራችንን ስለሚያጎድሉ እንጂ...


አንዳንድ ወዳጅነቶች ሳቢ ሊሆኑ ይችላሉ... ሃሴታችንን ግን ሊያጎድሉ ይችላሉ... 


አንዳንድ ስራዎች የክብር ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ... ግን ደግሞ መንፈሳችንን የሚቀይዱ ሊሆኑ ይችላሉ... 


ልምምዳችን ቅጽበታዊ ደስታን ይቸር ይሆናል... መንፈሳችንን ግን እያጠለሸ ይሆናል...


አንዳንድ በሮች ሳይከፈቱ ሊቀሩ ይገባ ይሆናል... ለአንድ ትልቅ አዳራሽ መከፈት ምክንያት ስለማይሆኑ ግን አይደለም - ምናልባት አዳራሹ የባዶነት፣ ያለመስከን፣ የጥፋት አዳራሽ ስለሚሆን እንጂ...


አንዳንድ ጊዜ በወርቅ የተጌጡ ጠረጴዛዎችን ትተን እንነሳ ይሆናል... ምግቡ መራር ስለሆነ ግን አይደለም - ምናልባት የማዕዱ ዋጋ የአዕምሮአችን ሰላም ማጣት ስለሚሆን እንጂ...


ዓለም ብዙ ለጆሮ ጣፋጭ የሆኑ ዝማሬዎች የሞላት ልትሆን ትችላለች... ልብን የሚመርዝ ሰንኮፍ የላትም ማለት ግን አይደለም...


እንደ ጸሐይ የሚያበራ ፈገግታ በዙሪያችን ሞልቶ ይሆናል... ምናልባት ግን ሲቀርቡት እንደ እሳት የሚያነድ ሊሆን ይችላል...

.
.
.

____

ጠቢብነት እያንዳንዱን ውበት ማሳደድ አይደለም - የትኛው ውበት ምን ዓይነት ወጀብ ውስጡ እንዳቋተ መለየት እንጂ...


ብልሁ ሰው - አማላይ፣ ቀዝቃዛና ነፋሻማ ከሆነው የውጭ ገጽታ መስኮቱን ዘግቶ የሚርቀው የውብ ገጽታው ጥላ ሆኖ ወደ ቤቱ ከሚገባ ስቃይ ለመዳን ነው...

____

ብስለት እያንዳንዱ ብርሃን ሙቀት እንዳልሆነ መማር ነው... ሁሉም ውበት በረከት እንዳልሆነ ማወቅ ነው... ከየትኛው እሳት ዳር መቀመጥ፣ ከየትኛው ደግሞ መራቅ እንዳለብን መገንዘብ ነው...


[ምክንያቱም የአዕምሮ ሰላም ከውጭ ከምናየው ገጽታ በላይ ውብ ነው...]


የኋላ ኋላ - በኑረታችን ውስጥ ልዩነት የሚፈጥረው በስንት ዓይነት ውበት መራጨታችን ሳይሆን በምንያህል የልቡና ሰላም ሩጫችንን መቋጨታችን ነው...

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

ባለፍሽበት መንገድ የረጨሽው ሽቱ ቅንጣቱ አልሳሳም - በሄድሽበት ስሄድ 'ውድህ በዚህ አለች' የሚል ጣፋጭ ጠረን ደርሶ ያጅበኛል...


የፃፍሽልኝ ደብዳቤ ሃሳብ ዛሬም አልደበዘዘም - አጠገቤ እንዳለሽ ሁሉ በፍቅር ቃና ያወጋኛል... 


የሰማናቸው ዜማዎች ለዛ በየማለዳው አዲስ ነው... ከርመው ልክ እንደ ወይን ሁሌም ይጥሙኛል... 


የሳቅሽ ገደል ማሚቶ በሕዋው ላይ እንደታዘለ ንፋስ ነው - በሄድኩበት ሁሉ ሲስረቀረቅ ይሰማኛል...


ዓይኖችሽን የተዋሱ ከዋክብት በየመዳረሻዬ ያበራሉ - በሌለሽበት ጎዳና ምሽቴን ይጋሩኛል...


ያኔ የተቀመጥሽበት ሶፋ ቅድም እንደተውሽው ሁሉ ሙቀቱ ይሰማኛል... 


የግቢያችን ውሻ ስትመጪ እንዳየ ጭራውን ይቆላል...


የማዕድቤቱ ሽታ እንዳበሰልሽ ሁሉ መዓዛው ያውዳል... 


ከመስታወቱ ውስጥ ፊትሽን አያለሁ - ፊቴን ብቻ ማየት ድሮ አቁሜያለሁ...


ለስላሳ ኮቴሽን ዛሬም እሰማለሁ - ድምጹን ተከትዬ ዞር ብዬ አያለሁ...


ሻይ ያልቀዳሁበት ብርጭቆሽ ይሞቃል - በእንፋሎቱ መሃል ከንፈርሽ ይሳላል...


በጉዞዬ መሃል ጥላሽ ይታየኛል - ሳይቀድም ሳይከተል መንገድ ያጋፋኛል...


የምትወጂው መጽሐፍ ከፊቴ ይታየኛል - እያነበብሽው ነው? በዓይኖችሽ ሲገለጥ ድምጹ ይሰማኛል...


ከመተኛሽ በኩል ትራሱ ጎድጉዷል - ዓይኔ ባያይሽም ተኝተሽበታል...


____


እንደ ሰው ኖረሽ ብታልፊም ዳሩ ፍጥረትሽ የመልዓክ ነው - ሳትታይ መድመቅ፣ አለሽ ሲሉ መርቀቅ ተሰጥቶሻልና...

____

ዓይኑ ሌላ አያይም ለሚሉኝ መልሴ አንቺ ነሽ...


ባትኖሪም - አለሽ!!

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

ልብ ያላሉ ልቦች


የትናንቱ አዳም...

ከጥልቅ ሰመመኑ - ከእንቅልፉ ቢነቃ
ስጦታ ጠበቀው - ከነፍሱ ጠበቃ፤

የዕድሜ ልክ እውነቱ - ተከፍላ ካ’ጥንቱ
ከጎኑ አገኛት - ስጋ ደም አምሳሉ፤


                                          
እናም ያኔ...


የታደለች ሔዋን - ዓይን አዋጅ ሳይገላት
ዕድለኛው አዳም - መስፈርት ሳይበዛበት
ያለ አማራጭ ... መጥተው
እርሷ - ለእርስ ... ኖረው
አለፉ ተባዝተው!


                                          
ይብላኝ ለዛሬ አዳም - ይብላኝ ለሔዋኑ
ከዕልፍ እንስቶች መሃል - ለጠፋች መጠኑ
እኒህ ሁሉ ተባዕት - ዓይኖቿን ላልሞሉ


                                          
እርሱ...

ዓይኑ ውበት ሲያሳድድ
ፈራሽ ገላ ማርኮት፣

                                          
እርሷ...

ልቧ ‘ብር...’ ስትል
ንዋይ ቀልቧን ነስቷት፤

 
ይኸው አሉ ዛሬም - የኔ ’ሚሉት አጥተው
ልብን ከልብ ውስጥ - አላሳድር ብለው፡፡

 
____


[ይህች ግጥም ከተጫረች ትንሽ ቆየች፤ ሰሞኑን ብዙ እየተነገረለት ያለውን 'Materialists' የተሰኘ ፊልም ሳይ ድንገት ትዝ ብላኝ ተጋራሁዋችሁ... በዚህ አጋጣሚ ፊልሙን እንድታዩት እመክራችኋለሁ...]

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

ዝንብን ያቆሸሻት ተፈጥሮዋ አይደለም፣ ውሎዋ እንጂ።

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

___

ከፍ ባልን ቁጥር... 'ከስር የሚገፉን አልያም ከላይ የሚስቡን ስላሉ ነው' ብለን አስበን እናውቃለን?

'ከትናንት የተሻለ ዕይታ የኖረን - በተሸካሚዎቻችን ትከሻ ስለተንጠላጠልን እንጂ በራሳችን ጉልበት ስለቆምን አልነበረም' ብለን እናውቃለን?

ከእጅ ያለው - የኖረን፣ የደረስንበት - የተገባን፣ ጉድፍ ይሁን እልፍ -  የከበበን፣ ደቆም ይሁን ልቆ - ያደመቀን... ሌሎች ስለነበሩ ነው ብለንስ እናውቃለን?
__

የእውነት ይህ ጉድለታችን ነው!!...

__

ስንቴ... 

          ✍ የተራዱንን እጆች ገፋን?

ስንቴስ...

          ✍ ከፍ ያደረጉንን ትከሻዎች ረገጥን?

ምን ያህል ጊዜ...

          ✍ ያጎሉንን ሃሳብ ባለቤቶች አደበዘዝን?

ለስንተኛ ጊዜስ...

          ✍ ተሻግረን ስናበቃ ያሻገረንን ድልድይ ሰበርን?

___

"Someone is sitting in the shade today because someone planted a tree a long time ago" ~ Warren Buffet

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

[History doesn’t wait for applause or agreement; it moves on with those who dare to be true.]

___

ታሪክ - ለባለታሪኮቹ እውነት እንጂ ለአንባቢዎቹ አስተያየት ቁብ አይሰጥም... ብትክደውም ሆነ ብትቀበለው እውነታውን ከመቀየር አንፃር  ሽራፊ አስተዋጽዎ እንደሌለህ ያውቃል...



🔥 ስሙን ብታጎድፍ - ግብሩን እንደማትደርስ ያውቃል... 


🔥 መልኩን ብታጠይም - ፍጥረቱን እንዳትደግም ያውቃል... 


🔥 በአፍህ ብትክደው - ከሕሊናህ እንደማትፍቀው ያውቃል... 


🔥 ማደሪያውን ብታጠፋ - አዳሪውን እንደማትገፋ ያውቃል...


___


ወዳጄ... የሆነን መካድ መሆኑን አይፍቅም!... ላለመስማት መሻት መዘከሩን አያስቀርም!... ምልክቱን ማጥፋት መንፈሱን አይከድንም...


“Truth is like the sun. You can shut it out for a time, but it ain’t goin’ away.” — Elvis Presley


መፍትሔው...


👉 ከነበር ስህተት ለነግ ብልሃት መቅዳት

👉 በእልፊት ከመቆጨት የተሻለ መስራት

👉 ለመልካም ጅማሬ የምስጋና ፍሬ - መዝራት ነው...

___

ዳይ...


ድርሻህን ኑር!!

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

አንብቤው እንዳልገባኝ መስመር - ፊትሽን ደጋግሜ እንዳየው የሚጎትተኝ መግነጢስ ምን ይሆን?...



የእናቱን ጡት 'ጠገብኩ' ብሎ እንደማይተው ሕፃን... ቆሎ 'በቃኝ' ብሎ እጁን ወደ ሌማት መዘርጋት እንደማይሰለች ሰው... 



በስንኞች መሃል ሲመላለስ በድግግሞሹ ልክ አዲስ የምስጢር ቋት እንደሚከፍት ጠቢብ... ከተራ መስመሮች መሃል የጠለቀ ሃሳብ፣ የረቀቀ ውበት፣ ያረመመ ቅኔ እንደሚፈለቅቅ ትጉህ አንባቢ - ፎቶሽ ሰርክ አዲስ የሚሆንብኝስ ለምንድነው?... 



ዕጹብ ነው... ድንቅ ነው...



በዝምታ፣ በጸጥታ፣ በእርጋታ ውስጥ ሆኖ ቅኔውን ያራቅቃል... በኃይል፣ በግርማ፣ በመርዕድ ዘዬ ሰምና ወርቁን ያፈልቃል...
 


[ደጋግሜ ባየሁት ቁጥር...]



አዲስ ውበት፣ አዲስ ጸዳል፣ አዲስ ሞገስ፣ አዲስ ስለት እያቀበለ ልቤን ይቦረቡራታል...



ቁራኛዬ...



ምን ይሉት መግነጢስ ነው ከፎቶሽ ስር እያጣደፈ፣ እያክለፈለፈ፣ እየሳበ የሚወስደኝ?...



Desktop እና Laptop ላይ Screensaver... ስልኬ ላይ Lock screen እና Home screen Wallpaper... Wallet ላይ፣ Album ውስጥ፣ ጠረጴዛዬ ላይ... [አልበዛም?...]



አንቺዬ... የእስከዛሬው ኩራቴ 'ከቡና ውጪ ሱስ አያውቀኝም' ነበር... ውሸቴን ይቅር በይው - ከፎቶሽ ጋር ሱስ ይዞኛል...



የምር ግን...



በአካል ጥላሽ ብርታት ልቤ ቀልቡን ካጣ - ከፊትሽ ስቆም አጥንቶቼ ላለመቅለጣቸው ዋስትናዬ ምንድነው?...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

የማግኘትን ጥቅም ከማግኛው መንገድ ስህተት ጋር አላምታታም...

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

ሰላም ወዳጆች
--
ከዚህ ቀደም መንደራችን ውስጥ የሚገኙ ሦስት ምርጥ Digital magazines አስተዋውቄያችሁ እንደነበር አትዘነጉም… ዛሬ ውብ የስነጽሑፍ ስራዎች የሚስተናገዱበት ሌላ መጽሔት ላስተዋውቃችሁ ነው…

ቀለም ይባላል…

በስነጽሑፍ፣ በፍልስፍና፣ በግለ-ታሪክና በወጎች ያጌጠ መጽሔት ነው…

እስኪ ጎራ ብላችሁ፣ አዲሱን ቅጽ 1 እትም 3 መጽሔትና ሌሎች ቁምነገሮችን ከቀደሙ ህትመቶቻቸው ጋር ተቋደሱ…

/channel/kelemofficial

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

✨Dildiy's New Year Reflection✨


As the old year dissolves into silence, may we step into the new one not as travelers bound by calendars, but as seekers of the infinite—sparks in the great mystery of existence.


This year, let us see beyond the veils of yesterday and tomorrow, awakening to the sacred rhythm of Now.


May our laughter become cosmic music, our tears cleanse illusions, and our love expand like starlight across the sky of being.


Together, let us walk as companions of the unseen, remembering that every breath is a doorway, every meeting a mirror, and every step a return home—to the timeless truth within.


For us, a New Year is not the measure of time, but the unfolding of consciousness.

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

የቁጣ ግራ ቀኝ...

.
.
.

[፩]

___

ሰዎች በቁጡነት ይወቅሱሃል እንጂ ያስቆጣህን ሰው ነውር፣ አልያም ለኮስ ያደረገህን ውስጠ ነገር ልብ ብለው አይመረምሩም... በሌላ አገላለጽ ያስቆጡሃል እንጂ ያስቆጣህን ጸባይ ጥመት በአንተ ቦታ ቆመው አይመዝኑም...
 

በምን ተቆጣህ?... No one cares [እርሱ ያንተ ጉዳይ ብቻ ነው]... ሌላው ይህን ለመጠየቅ ጊዜ አያጠፋም... ለራሱ ሲሆን ትንሽ ነገር የሚበቃው ሁሉ አንተ ላይ ሲደርስ አንዳች አይሰማውም...


ብዙ ሰዎች በእነርሱ ሰበብ ባይሆንም እንኳ ተናደህ ሲያገኙህ ሊረዱህ ከመሞከር ይልቅ ምቾታቸውን እንደነሳህ ሊያስቡ ይችላሉ... ወይ ደግሞ እነርሱ ቢሆኑ ፈጽሞ የማያደርጉትን ነገር በምክር መልክ ሊለግሱህ ይሞክራሉ...


ንዴት፣ ብስጭት፣ ቁጣ ወዘተ - ጥሩ ነገር እንዳልሆኑ እኮ ታውቃለህ... ስሜትን መግዛት መሰረታዊ የኑሮ መርህ እንደሆነም አይጠፋህም... ግን ደግሞ ስሜት አለህ... ሰውም ነህ... ነገሮች ከገደባቸው ሲሻገሩ ምላሽ መስጠት መጀመርህ ተጠባቂ ነው... 


[ብስለት ማለት ለነገሮች ስሜት ማጣት ማለት አይደለም - ሚዛን መጠበቅ እንጂ...ብልህነት ይህን ስሜት መቆጣጠር እንጂ ዜሮ ማድረግ አይደለም... ምላሹን መመጠን እንጂ እንዳልተሰማው መሆን አይደለም... 'ምንም አይሰማኝም' ምናምን የሚል ደረቅ ስታገኝ ታዝበህ እለፈው...]


አንዳንዱ ገፍቶ፣ ገፋፍቶ፣ ገፍትሮ ከብስጭት ጫፍ ያደርስህና React ማድረግ ስትጀምር በተራው መናደድ ይጀምራል... እንዴ 'ቅቤ እየቀባህ' ነበር እንዴ የመሰለው?...


ለመከፋትህ፣ ለብስጭትህ፣ ለንዴትህ ነዳጅ ሲጨምር መቆየቱን ሳይሆን በነዳጁ ብዛት መቀጣጠል መጀመርህን ነው ሰው የሚያስተውለው... ነገሩ የሆነበትን ምክንያት ሳይሆን የሆነውን ክስተት ብቻ ነው የሚመለከተው... ይህ ዓይነት ሰው ለፍርድ ቅርብ ነው... የደረሰበት ላይ ሆኖ ውሳኔ ይሰጣል... ከመነሻው ደርሶ አይመረምርም... ከመድረሻው ዘልቆም አያመሳክርም... ጭራሽ ሰው መሆንህን ይረሳዋል... ስሜትም ያለህ አይመስለው...


በእርሱ ቤት ሲቀዳልህ የቆየው ነዳጅ ተራ ውሃ ነበር... 'ደግሞ ይሄ ምን ያናድዳል?' ይልሃል... [አይገርምም?... እዚህ ጥግ ድረስ ለሌሎች ስሜት እናጣለን]... 'አካበድከው' ይልሃል... 'Emotional intelligence ላይ መስራት አለብህ' ምናምን የሚልም አይጠፋም... በሌላ ቀን ያንተን ቁራጭ በማትደርስ እንከን ሲብከነከን ብታገኘው ታዲያ አይግረምህ... 


[እኛ ከሌሎች ስንክሳር በላይ የራሳችን ስንጥር ዘልቆ የሚሰማን ግለኞች ነን]


መረሳት የሌለበት...


ሁላችንም ቅኝታችን ለየቅል ነው... ተመሳሳይ ነገሮች እኩል ስሜት አይሰጡንም... አንድ ዓይነት ነገሮች እኩል አይነዝሩንም... ለብግነትህ ምክንያት የሆነ ነገር ለእኔ ቁብ ላይሰጠኝ ይችላል... እኔን ያስደነገጠ ጉዳይ አንዳች ስሜት አይፈጥርብህ ይሆናል... [በዚህ ረገድ ልዩ ልዩ ነን]

___

[፪]
___

ቁጣህን በማሰሮ ውስጥ እንደሚንተከተክ ወተት ብታፍነው ጊዜው እየገፋ ሲመጣ መገንፈሉ አይቀርም... ስለዚህም መተንፈስ አለበት... የታፈነ፣ የታመቀ፣ የተወጠረ ነገር በራሱም ሆነ በሌላው ላይ ጉዳት ከማምጣት አይመለስም...


"ድስት ቢገነፍል የሚያቆሽሸው ራሱን ነው" ቢባልም ፍንጥርጣሪው ልብስ አያበላሽም ማለት አይቻልም...


እርግጥ ነው - ቁጣ የማይፈለግ ስሜት ነው... ከዚያ በላይ ግን ቁጣን አምቆ መቆየት እጅግ አደገኛ ነገር ነው... Buddha እንዳለው: 


“Holding on to anger is like grasping a hot coal with the intent of throwing it at someone else; you are the one who gets burned.”


ለዚህም ሲባል ቁጣን በልኩ ማስተናገድ፣ ከልብ ማዳመጥ፣ ምንጩን መመርመር፣ ቆስቋሽ ሰበቡን መለየት፣ ከምንም በላይ ደግሞ [በራስ ላይ መንቃት] እጅግ ጠቃሚ ይሆናል...


በመሰረቱ ስሜቶቻችን ጠላቶቻችን አይደሉም - ምልክቶች እንጂ... አንዳንዴ ቁጣ የጥልቁ እኛነታችን ባሕሪያዊ ጥላ ሊሆን ይችላል... በስውሩ የአዕምሮአችን ክፍል ውስጥ ያለውን ጠቋሚ መስታወት... በዚህ አውድ መምህር ሲሆን በቅጡ ለማያነበው ደግሞ የአዕምሮ ገዢ ሆኖ እውነታን ይከልላል - ያስክዳልም...


እናም ስሜቶቻችንን በማፈን ጠቢብ አንሆንም... በአንክሮ በማዳመጥ እንማርባቸዋለን እንጂ...

_

እናም እንዲህ እንላለን...


ለሌሎች ብሽቀት ምክንያት አለመሆን ደግ ነገር ነው... ሲናደዱ ለመረዳት መሞከር ደግሞ ሩሕሩሕነት ነው... ስሜት አለማመቅ ጠቃሚ ነገር ነው... በስሜት መስታወት ውስጥ ውስጠትን ማየት ደግሞ ዘላቂ መላ...

___

እነሆ ነገራችንን በሚዛን የሚጠቀልልልን የጠቢብ ቃል...

___

“Anybody can become angry — that is easy. But to be angry with the right person, to the right degree, at the right time, for the right purpose, and in the right way—that is not within everybody's power and is not easy.” – Aristotle

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

🌿

🌿

🌿

ፍቅሬን እንዴት ማሳየት እንዳለብኝ ተለማምጄ ሳልጨርስ ሄደች...


በልቤ ውስጥ ያለው ነበልባል በቃል ተሰርቶ ወደጆሮዋ ሊፈስ ይቃትት ነበር... የመውደዴ ብርታት በቃል አክናፍ በርሮ እዝነ ልቡናዋን ሊያንኳኳ ይጓጓ ነበር... ጎርፍ የመውረጃ ፈለጉን እንደሚያስስ... ሕፃን የእናቱን ጡት ፍለጋ በጨለማ እንደሚዳብስ...


በውስጤ የታመቁት ቃላት ከውክብክቡ ዓለም አይደሉምና በተራ ድምጽ አይወከሉም - በጸጥታ ይነግሳሉ እንጂ... መሻቴ ከአፍዓ ገጽዋ አልተቀዱምና ለሙገሳ የተሰሩ ፊደላት አልሰጠሁዋትም - በጥልቅ ዝምታዬ ውስጥ የሚጓደዱትን እንጂ... 


[በቅጽበታት መሃል እንደሚገኝ ትንፋሽ... ነፍሶች እንደሚያወጉበት ድምጽ የሌለው ፈሳሽ...]


አዎን - እኔ ይህን ጸጥታ ወደ ቋንቋ መለወጥ ገና አልተማርኩም ነበር... እርሷም እንዲህ ዓይነት ቋንቋ ሰምታ አታውቅም ነበር...


ሄደች... 


እውነቱን ከመግለጼ በፊት ተጨለጠች... 


[ፍቅር] 


የምሰጣት - የኔ 'ምለው፣ የምትነፍገኝ - የእርሷ የሆነው እንዳልሆነ ሳልነግራት በነነች...


የዘላለማዊው ኃይል መስታወት፣ በሁለንታ ላይ የሚፈስ የኃይል ዥረት መሆኑን ሳላስታውሳት ዱካዋን አጠፋች... ዳናዋን ሰወረች...


ሄደች... የአካል ኑረቷን ከለለች...


[አዎን ሄዳለች - ግን ደግሞ አልሄደችም...] 


መቅረቷ በሌላ ቅርጽ መኖር ሆኖ ቀጥሏል... አካሏን እንጂ በኔ ዓለም ውስጥ ያነቃችውን ፍቅር በቀላሉ ማጥፋት ስላልተቻላት በመንፈስ ነብራለች... 

 🌿

ፍቅሯ ወደ ኁልቆ አልባው ዓለም ሲያሻግረኝ ከፈራሽ ገላዋ ብፋታም በእርስዋ ሰበብ የተሰጠኝ ማሕተም የሃገሩን ኬላ ሁሉ የሚያሻግር አርነት ሰጥቶኛል... 


[በእውኑ የተወኝ ምኗ ነው?...]

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

ያገኙሽ ሁሉ በአንቺ ምክንያት የውበት መለኪያ ሚዛናቸው ተደነቃቀፈ... ትናንት 'የውበት ጥግ' ካሏት ጋር ሲያነፃጽሩሽ አልደራረስ አልሽና - አልቀው ሰቀሉሽ... 


በእውነት ከዚህ ከፍታ ላይ ሌላ ሴት አይደለም አንቺ ራስሽም መድረስሽን እጠራጠራለሁ...


ውበትሽ ምን እንደሆን ታውቂያለሽ?...


መረዳትሽ!!

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

[ግራ እየገባኝ ስሄድ አንድ ነገር እየተማርኩ እንደሆነ አውቃለሁ... ምናልባትም ለመንገዴ አንድ ተጨማሪ የብርሃን አምድ እየተተከለች ይሆናል...]

.
.
.

አንዳንዴ ተራ ብዬ ባቃለልኩት ነገር ውስጥ ተቆጥሮ የማያልቅ መደነቅ ይወርሰኛል... ሌላ ጊዜ ደግሞ ድንቅ ያልኩትን ሳሳድድ ከእጄ ያለውን ውበት አጣና ሃዘን ይከበኛል...


[ወደላይ ብቻ የሚያዩ ከእግሮቻቸው ስር ያለውን የምድር ሃብት አይረዱም... አዘቅዝቀው የሚመለከቱም ከበላያቸው ያለውን ንጽህና አይገነዘቡም...]

___

አንዳንዴ ብዙ አለኝ ያልኩትን ጊዜ በአልባሌ ነገር ሞልቼ አባክነዋለሁ... አጠረኝ ያልኩትን ደግሞ ከበድ ባሉ ስራዎች አጭቄ ሳልጠቀም ፈጀዋለሁ...


በሁለቱ መካከል የሚተርፈኝ አንዳች የለም - ከጭንቀትና እረፍት አልባነት ውጭ...


[ነገ ይሆንልኛል እያሉ የሚጠብቁ ዛሬን አያጣጥሙም... ዛሬ ካልሞላልኝ ብለው ሙጥኝ የሚሉም ከነግ ተስፋ አይገናኙም...]

___


አንዳንድ ቀን በፍቅር እንደተጥለቀለቅሁ ይሰማኛል - ሆኖም ወዲያው በእውር ድንብር አስረክቤው ዝምታ ይውጠኛል... ሌላ ጊዜ ደግሞ ፍቅር አጣሁ ብዬ ፍለጋ እወጣለሁ - ይሁንና ቅንስናሽ ማንነቴን በየቦታው ተቀምጦ ሳገኘው እደነግጣለሁ...


በዚህ ሰበብ የሃሳብ ድካም ያናውዘኛል... ውርሱ ሃዘን የሆነ ዘር በውስጤ ያጎነቁላል...


[መፈቀርን ብቻ የሚሻ መስጠትን ሳይማር ያልፋል... ፍቅር ሲሰጥ ብቻ የኖረም የመቀበል ቆምታን ይተላለፋል...]

___


የሕይወት መትረፍረፍ በተሰማኝ ማግስት ራሴን የሚጠፋ ጥላ ሲያሳድድ አገኘዋለሁ... ኑረት በጉድለት ስሜት ስትከበኝ ደግሞ ጫፍ በሌለው ምኞት ሸክሟን አበዛዋለሁ...

በዚህ ሰበብ ባዶነት ይወርሰኛል... ተስፋቢስነት ይጫነኛል...


[መድረሻውን ብቻ የሚያይ ጉዞውን ይረሳል... መንገዱን ብቻ ሙጥኝ ያለ አድማሱን ይዘነጋል...]

___


ነፃ የሆንኩ ይመስለኛል - ግና ራሴን የማገኘው በምርጫዎች ሰንሰለት ታብቶ ነው... ነፃ እንዳልሆንኩ አስባለሁ - ግና ውስጤ የማየው የግዞት ጫና የማይታከካቸውን ዕልፍ ቦታዎች ነው...


በዚህ ሰበብ ቀልቤን ቅዥት ሞልቶት ያታልለኝና የምር ትግል ውስጥ እገባለሁ...


[ነፃነትን የሚፈሩ የራሳቸው አዕምሮ እስረኛ ከመሆን አይድኑም... ነፃነትን ያለአግባብ የሚጠቀሙ የምኞቶቻቸው ባሪያ ከመሆን አይቀሩም...]

___

እንደነገርኳችሁ ነው...


ግራ እየገባኝ ስሄድ አንድ ነገር እየተማርኩ እንደሆነ አውቃለሁ... 

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

ያልገለጽኩት ፍቅር እንደተዳፈነ እሳት ነው... ውስጥ ውስጡን በጸጥታ ያኝከኛል... መንደርተኛው ፍሜን አያይም፣ ምክንያቱም ማንደጃው ያለው ከልቤ ውስጥ ነው...

-

ይቅርታ ያልጠየቅሁበት ስህተት እንደ ሃረግ ቅጠል ነው... በሃሳቤ ላይ ተንጠላጥሎ ይመነደጋል... ጸጥ ረጭ ባለ ለሊት ሳይቀር የምሬት እንጉርጉሮውን እያመላለሰ ይረብሸኛል...

-

ያልገለጽኩት ምስጋና የደረቀ ምንጭ ይመስላል... ካዳፈንኩት ቦታ መውጫ አጥቶ በጊዜ ብዛት ጣዕም አጥቷል... በመንገዴ ላይ አኮቴት የሚገባቸው ቢኖሩም ንፉግ ሆኜ እታያለሁ...

-

በአንድ ወቅት የቀበርኩት እውነት በጎድኖቼ መሃል እረፍት እንዳጣች ወፍ ይርገበገባል... ክንፎቹን እያማታ ክፍቱን ሰማይ ይናፍቃል... የውስጤ ህመም ቢበረታም ሃፍረት እንዳነቀኝ አለሁ...

-

የሰሰትኩት ጉልበት እንደ ድንጋይ ይከብደኛል... ብልጥ የሆንኩ መስሎኝ ስለግም ድልብ አድርጎ  ያመኛል... ልቤን ሲያፍናት መተንፈስ ጭንቄ ነው...

-

የነፈግሁት ርህራሔ ጸሐይ እንዳጣ ፍሬ ወይቧል... የጨከንኩባቸው ዓይኖች ሳይኖሩ ያዩኛል... ብቻዬን ብሆንም መንፈሴን የሚያድን አሳዳጅ አጥቼ አላውቅም...

-

በሌሎች ላይ ያዘነብኩት ጉዳት ከቀብር እንደሸሸ መንፈስ በሕልሜ አውድ ይቅበዘበዛል... በቁርና ሃሩር መሃል ያነጉደኛል... የበዳይነት ሕመም ዘልቆ ይሰማኛል...

-

የሰው ልጅ በብዙ የጦር አውዶች የሚባትል መደበኛ ተዋጊ ነው...

.
.
.

✍ ይቅርታ የማድረግ ጦር ሜዳ - የበደሉን እጆች መተው፣ ጉዳታቸው ባልሻረበት እንኳ ሁኔታ...


✍ እውነትን የመናገር ጦር ሜዳ - ዝምታ የደህንነት ምልክት በሚመስልበት ጊዜ ሁሉ...


✍ ደግ ሆኖ የመዝለቅ ጦር ሜዳ - መራርነት ምቹ መንገድ በሆነ ጊዜ ጭምር...


✍ የአሁናዊነት ጦር ሜዳ - እልፊት እያፏጨ በሚያጸጽትበት፣ መፃዒ እየጠራ በሚያሰጋበት ጊዜ ሳይቀር...


✍ የመተው ጦር ሜዳ - የማይመለስ አመድ፣ የማይመጣ ዘመድ፣ መሆኑን ሳይመዝኑ ጭምር...


✍ ዳግም በወዳጅነት የማመን ጦር ሜዳ - ቃል በተበላበት፣ እምነት በተናደበት ጊዜ እንኳን...


✍ ተስፋን ሕያው የማድረግ ጦር ሜዳ - ጨለማ የመዳሰስ ያህል በገዘፈበት ጊዜ ሳይቀር...

____

እስኪ ንገሩኝ... 

[ሰው በምድር ላይ ቆሞ ይሄድ ዘንድ ስንት የጦር ሜዳ ነው ማሸነፍ ያለበት?... በልቡና ውስጥ ያለ ሰይፍ በእጅ ከጨበጡት በላይ አይወጋምን?... በሕሊና ውስጥ ያለስ ጦርነት በገሃድ ካለው አይልቅምን?...]

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

☂☂☂

ገጣሚ - ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን

☂☂☂

አንባቢ - ገጣሚ ነብይ መኮንን

☂☂☂

ርዕስ - እንኳን ለዓመት ጉድ አበቃን!

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

ከቅኔ ወርቁን ላዋልድ - የሰሙን ሽፋን ጠርጌ
የዘመን ስልቱን ላወጋ - ከ[አ]ደባባይ ሸሽጌ፤

.

ለእኔዬ እኔው ልናገር - እኔዬን እኔው [ላ]ርቀው
ከወዳጅ አልፎ ሂያጅ ሃሜት - ቢያተርፈኝ ላስጠነቅቀው፤

.


'ካለቃ ምንዝር ግርግር - ከአስመሳይ ሌጣ ፈገግታ
ከተንኮል ከክፋት ግብሩ - ከሰው ልጅ የአፍ ወለምታ

መዳኛ - ላወጋው መላ
ልሰጠው - ጋሻ ከለላ

ላርቀው - ከነገር ጠለል
ላመጥቀው - በጠቢብ ብሂል

እኔዬን - እኔው ላድነው
ከቦታው - ድንገት ብነቅለው

.
.
.

እኔዬን ከኔ አጣሁት - ለኔዬ ማን ይናገረው?

___

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

ግትርነት የሚያውቁትን መላ ላለመተግበር፣ የማያውቁትን ብልሃት ላለመጠየቅ የሚያዝ አቋም ነው።

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

"Mankind must put an end to war before war puts an end to mankind." ~ John F. Kennedy

___

የሰው ልጅ የውድቀቱ ጥግ፣ የድንዛዜው ቁንጮ፣ የኋላቀርነቱ መስታወት...


ጦርነት!!!


"I know not with what weapons World War III will be fought, but World War IV will be fought with sticks and stones." ~ Albert Einstein


ሰልጥነን እንደ ሰየጠን፣ ዘምነን እንደ ጎመዘዝን የሚናገርብን እውነት... 

በቁስ ተጊጠን በመንፈስ እንደነጠፍን የሚያሳብቅ ገጽታ....

በሳይንስ ተራቀን በሞራል እንደቀነጨርን መስካሪ ሃቂቃ...


ጦርነት!!...


የሰው ልጅ የትኛውንም ዓይነት አመክንዮ ቢደረድር፣ የትኛውንም ዓይነት ሰበብ ቢያግተለትል ልክ የማይሆንበት ተግባሩ የጦርነት ግብሩ ነው...


ድህነት ጦርነት አይቀሰቅስም - የሌጣ አዕምሮ ግልፍተኝነት ግን ጠብ ጭሮ ሌማት ያራቁታል...


'የድንበር መገፋት' ጦር አያሳብቅም - የብልሃት አልባ ችኩል ግብር ግን የእግር መቆሚያ ይነጥቃል...


የሃሳብ ልዩነት ሳንጃ አያማዝዝም - የአምባገነን ግትር አቋም ግን የቂም እርሾ ይወልዳል...


ኢጎህን መግደል አቅቶህ ሰው መግደል የቀለለህ ዕለት ያኔ አንተ ቀለሃል!... 


እናም - እነሆ ቃል...


ማኔ - ቴቄል - ፋሬስ!!

__

"The greatest victory is that which requires no battle." ~ Sun Tzu 'The Art of War'

__


'የዘመነ' የጦር መሳሪያ መስራትህ ዘመናዊ አያደርግህም - ከንቱነትህን ያሳብቅ እንደሁ እንጂ...



ራስን የማሸነፊያ ብስለት ስለሌለህ ሌሎችን የምታጠቃበት ሰይፍ መሳልህ ጠቢብ አያደርግህም - ጦረኛ እንጂ...



በጠብመንጃህ ነድተህ የፈጠርከውን ጠብ ቢሸሽ ፈሪ አይባልም - ስሜት ከሚነዳው ጋር የማይታገል ብልህ እንጂ...



ፍርሃትህን የምትገራበት መላ ስለሌለህ ሌሎችን በፍርሃት ውስጥ የሚከት ጠብመንጃ ታከማቻለህ...



በራስህ ዓለም የሁልጊዜ ባለስልጣን የመሆን ክህሎት ሲያጥጥህ - ተሰባሪ ወንበር ለማስጠበቅ ለጋ ሕልም ትሰብራለህ...

____

No More War!!

I do not like war—  
I know what it makes us:  
Children lost to the storm,  
Mothers weeping in vain.  

Houses turned to ash,  
Hope a fleeting spark,  
Future crushed to dust,  
Revenge left in the dark.  

Power feeds the flame,  
Lives cut short, unnamed—  
This is my plea, my cry,  
No more war—we don’t deserve to die.  

(Humble words from one who sees,  
A world aching for peace.)

____

@bridgethoughts

Читать полностью…

ድልድይ | Dildiy | Bridge

.
.
.

ውዴ
_

ሞትሽ በልቤ ውስጥ ያለውን መውደድ አልገደለውም፤ 
መለየትሽ ከነፍሴ የታተመውን ፍቅር አልፋቀውም፤ 
_

አብረሽኝ ባትሆኚ አብሮኝ የሚኖረውን አክብሮት የሚነጥቀኝ የለም፤
በስጋ ባናብርም በመንፈስ የምንቆራኝበትን እውነት አልተሰረቅንም፤ 
_

በአካል ባናወራም በቀልባችን የምንግባባበትን አቅም ሜዳ አልጣልኩም፤ 
በድምጽ ባልሰማሽም ከዕዝነ-ልቡናዬ ታትሞ በየመዓልቱ የሚያዜም ቀናነትሽን ዝም አላስባልኩም፤
_

ዕጣሽ ዕጣዬ ሆኖ እስክንመሳሳል የአካል ንጥለትሽን ጉዳት በመንፈስ ተቋልፎሽ ውበት እያደስኩ እኖራለሁ።
_

የኔ ውድ 🌺

____

@bridgethoughts

Читать полностью…
Subscribe to a channel